ዘፀአት 34:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ትቆራርጣላችሁ።+ ዘዳግም 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+ ዘዳግም 16:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ለአምላክህ ለይሖዋ በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የማምለኪያ ግንድ*+ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ አትትከል።
3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+