መሳፍንት 16:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 የፍልስጤም ገዢዎች “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን!” በማለት ለአምላካቸው ለዳጎን+ ታላቅ መሥዋዕት ለመሠዋትና ለመደሰት አንድ ላይ ተሰብስበው ነበር። 1 ዜና መዋዕል 10:8-10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።+ 9 ስለሆነም ሳኦልን ገፈፉት፤ ራሱን ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከወሰዱ በኋላ ወሬው ለጣዖቶቻቸውና+ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ወደ ፍልስጤም ምድር ሁሉ መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአምላካቸው ቤት* አስቀመጡት፤ ራሱን ደግሞ በዳጎን ቤት+ ላይ ቸነከሩት።
23 የፍልስጤም ገዢዎች “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን!” በማለት ለአምላካቸው ለዳጎን+ ታላቅ መሥዋዕት ለመሠዋትና ለመደሰት አንድ ላይ ተሰብስበው ነበር።
8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።+ 9 ስለሆነም ሳኦልን ገፈፉት፤ ራሱን ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከወሰዱ በኋላ ወሬው ለጣዖቶቻቸውና+ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ወደ ፍልስጤም ምድር ሁሉ መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአምላካቸው ቤት* አስቀመጡት፤ ራሱን ደግሞ በዳጎን ቤት+ ላይ ቸነከሩት።