-
1 ሳሙኤል 8:11-18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 እንዲህ አላቸው፦ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው ንጉሥ እንዲህ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት አለው፦+ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ+ ሠረገላው ውስጥ ያስቀምጣቸዋል፤+ ፈረሰኞችም+ ያደርጋቸዋል፤ የተወሰኑትንም ከሠረገሎቹ ፊት ፊት እንዲሮጡ ያደርጋል። 12 ለራሱም የሺህ አለቆችንና+ የሃምሳ አለቆችን+ ይሾማል፤ አንዳንዶቹም መሬቱን ያርሳሉ፣+ እህሉን ያጭዳሉ+ እንዲሁም የጦር መሣሪያዎቹንና ለሠረገሎቹ+ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይሠራሉ። 13 ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ቅባት ቀማሚዎች፣* ምግብ አብሳዮችና ዳቦ ጋጋሪዎች+ ያደርጋቸዋል። 14 እንዲሁም ከማሳችሁ፣ ከወይን እርሻችሁና ከወይራ ዛፎቻችሁ+ ምርጥ የሆነውን ይወስዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይሰጣቸዋል። 15 ከእህል ማሳችሁና ከወይን እርሻችሁ ላይ አንድ አሥረኛውን ወስዶ ለቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣል። 16 ወንድ አገልጋዮቻችሁንና ሴት አገልጋዮቻችሁን፣ ከከብቶቻችሁ መካከል ምርጥ የሆኑትን እንዲሁም አህዮቻችሁን ይወስዳል፤ ለራሱ ሥራም ይጠቀምባቸዋል።+ 17 ከመንጋችሁ መካከል አንድ አሥረኛውን ይወስዳል፤+ እናንተም የእሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ። 18 ለራሳችሁ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሳ የምትጮኹበት ቀን ይመጣል፤+ ሆኖም በዚያ ቀን ይሖዋ አይመልስላችሁም።”
-