ኢያሱ 7:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ከዚያም ኢያሱ “ወጥታችሁ ምድሪቱን ሰልሉ” በማለት ከቤቴል+ በስተ ምሥራቅ በቤትአዌን አቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ጋይ+ ሰዎችን ላከ። በመሆኑም ሰዎቹ ወጥተው ጋይን ሰለሉ። ኢያሱ 18:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የመጀመሪያውም ዕጣ ለቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ፤ በዕጣ የደረሳቸውም ክልል በይሁዳ ሰዎችና+ በዮሴፍ ሰዎች+ መካከል የሚገኘው ነበር። 12 በሰሜን በኩል ያለው ወሰናቸው ከዮርዳኖስ ተነስቶ በስተ ሰሜን ወዳለው የኢያሪኮ+ ሸንተረር ይወጣና በስተ ምዕራብ ወደ ተራራው ያቀናል፤ ከዚያም ወደ ቤትአዌን+ ምድረ በዳ ይዘልቃል። 1 ሳሙኤል 14:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤልን አዳነ፤+ ውጊያውም እስከ ቤትአዌን+ ድረስ ዘለቀ።
2 ከዚያም ኢያሱ “ወጥታችሁ ምድሪቱን ሰልሉ” በማለት ከቤቴል+ በስተ ምሥራቅ በቤትአዌን አቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ጋይ+ ሰዎችን ላከ። በመሆኑም ሰዎቹ ወጥተው ጋይን ሰለሉ።
11 የመጀመሪያውም ዕጣ ለቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ፤ በዕጣ የደረሳቸውም ክልል በይሁዳ ሰዎችና+ በዮሴፍ ሰዎች+ መካከል የሚገኘው ነበር። 12 በሰሜን በኩል ያለው ወሰናቸው ከዮርዳኖስ ተነስቶ በስተ ሰሜን ወዳለው የኢያሪኮ+ ሸንተረር ይወጣና በስተ ምዕራብ ወደ ተራራው ያቀናል፤ ከዚያም ወደ ቤትአዌን+ ምድረ በዳ ይዘልቃል።