1 ሳሙኤል 16:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው። እሱም የቀይ ዳማ፣ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር።+ ከዚያም ይሖዋ “ተነስ፣ ቀባው፤ የመረጥኩት እሱን ነው!” አለው።+ 1 ሳሙኤል 17:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ሳኦል ግን ዳዊትን “አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፤+ እሱ ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነው፤ ስለዚህ ይህን ፍልስጤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው።