-
ዘሌዋውያን 11:23, 24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 አራት እግር ኖሯቸው ክንፍ ያላቸው ሌሎች የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 24 በእነዚህ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+
-
-
ዘሌዋውያን 15:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 “‘ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል፤ ይህ ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ነገርም ርኩስ ይሆናል። 5 የሰውየውን አልጋ የነካ ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+
-
-
ዘኁልቁ 19:16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 በሰይፍ የተገደለን ወይም በድንን ወይም አፅምን ወይም መቃብርን የነካ በሜዳ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።+
-