ዘሌዋውያን 2:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤+ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+ ዘሌዋውያን 6:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤+ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል።+ ዘሌዋውያን 10:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ+ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤+ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው። ዘኁልቁ 5:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “‘እስራኤላውያን ለካህኑ የሚያቀርቧቸው ቅዱስ መዋጮዎች+ በሙሉ የእሱ ይሆናሉ።+ ዘኁልቁ 18:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በእሳት ከሚቀርቡት እጅግ ቅዱስ የሆኑ መባዎች ውስጥ የሚከተሉት የአንተ ይሆናሉ፦ ለእኔ የሚያመጡትን የእህል መባቸውን፣+ የኃጢአት መባቸውንና+ የበደል መባቸውን+ ጨምሮ የሚያቀርቡት ማንኛውም መባ የአንተ ይሆናል። ይህ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው።
14 እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ+ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤+ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው።
9 በእሳት ከሚቀርቡት እጅግ ቅዱስ የሆኑ መባዎች ውስጥ የሚከተሉት የአንተ ይሆናሉ፦ ለእኔ የሚያመጡትን የእህል መባቸውን፣+ የኃጢአት መባቸውንና+ የበደል መባቸውን+ ጨምሮ የሚያቀርቡት ማንኛውም መባ የአንተ ይሆናል። ይህ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው።