የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 23:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 አምላክ እንደ ሰው አይዋሽም፤+

      እንደ ሰው ልጅም ሐሳቡን አይለውጥም።*+

      እሱ ያለውን አያደርገውም?

      የተናገረውንስ አይፈጽመውም?+

  • 1 ሳሙኤል 2:31-34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 በቤትህ እስከ ሽምግልና ድረስ በሕይወት የሚቆይ ሰው እንዳይኖር የአንተንም ሆነ የአባትህን ቤት ብርታት* የምቆርጥበት ቀን ይመጣል።+ 32 ለእስራኤል በተደረገው ብዙ መልካም ነገር መካከል በማደሪያዬ ውስጥ ተቀናቃኝ ታያለህ፤+ በቤትህም ዳግመኛ አረጋዊ የሚባል አይገኝም። 33 በመሠዊያዬ ፊት እንዲያገለግል የምተወው የአንተ የሆነ ሰው ዓይኖችህ እንዲፈዙና ለሐዘን እንድትዳረግ* ያደርጋል፤ ከቤትህ ሰዎች መካከል ግን አብዛኞቹ በሰዎች ሰይፍ ይሞታሉ።+ 34 በሁለቱ ልጆችህ በሆፍኒ እና በፊንሃስ ላይ የሚደርሰው ነገር ምልክት ይሆንሃል፦ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።+

  • ኢሳይያስ 55:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣

      ምድርን በማራስ እንድታበቅልና እንድታፈራ፣

      ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን እንድትሰጥ ሳያደርግ ወደመጣበት እንደማይመለስ ሁሉ፣

      11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ እንዲሁ ይሆናል።+

      ደስ የሚያሰኘኝን ነገር* ያደርጋል፣+

      የተላከበትንም ዓላማ በእርግጥ ይፈጽማል እንጂ

      ያላንዳች ውጤት ወደ እኔ አይመለስም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ