-
ዘኁልቁ 27:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 እሱም በኡሪም+ አማካኝነት የይሖዋን ፍርድ በሚጠይቅለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር ያሉት እስራኤላውያን እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ በእሱ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእሱ ትእዛዝ ይገባሉ።”
-
-
1 ሳሙኤል 23:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ስለሆነም ዳዊት “ሄጄ እነዚህን ፍልስጤማውያን ልምታ?” በማለት ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም ዳዊትን “ሂድ፣ ፍልስጤማውያንን ምታ፤ ቀኢላንም አድናት” አለው።
-
-
1 ሳሙኤል 23:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ታዲያ የቀኢላ መሪዎች* ለእሱ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? አገልጋይህ እንደሰማውስ ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ለአገልጋይህ አሳውቀው።” በዚህ ጊዜ ይሖዋ “አዎ፣ ይወርዳል” አለው።
-