27 ዳዊት፣ ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ ዘማሪዎቹ እንዲሁም ታቦቱን የማጓጓዙ ሥራ ኃላፊና የዘማሪዎቹ አለቃ የሆነው ኬናንያ እጅጌ የሌለው ምርጥ ልብስ ለብሰው ነበር፤ በተጨማሪም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።+ 28 መላው የእስራኤል ሕዝብ በቀንደ መለከት፣ በመለከትና+ በሲምባል ድምፅ ታጅቦ ባለ አውታር መሣሪያዎችንና በገናን+ ከፍ ባለ ድምፅ እየተጫወተ በእልልታ+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አመጣ።