-
1 ነገሥት 5:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “አባቴ ዳዊት ከተለያየ አቅጣጫ ጦርነት ይከፈትበት ስለነበር ይሖዋ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ለአምላኩ ለይሖዋ ስም የሚሆን ቤት መሥራት እንዳልቻለ በሚገባ ታውቃለህ።+
-
-
1 ዜና መዋዕል 17:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።+ 5 እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱም የማደሪያ ድንኳን ወደ ሌላው የማደሪያ ድንኳን* እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ 6 ከመላው እስራኤል ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ ሁሉ ሕዝቤን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የእስራኤል ፈራጆች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ፣ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?” ’
-