14 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ 15 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤+ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤ 16 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሻውሻ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። 17 የዮዳሄ ልጅ በናያህ የከሪታውያንና+ የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ከንጉሡ ቀጥሎ ዋና ባለሥልጣናት ነበሩ።