-
መሳፍንት 9:50-53አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
50 ከዚያም አቢሜሌክ ወደ ቴቤጽ ሄደ፤ ቴቤጽንም ከቦ በቁጥጥር ሥር አዋላት። 51 በከተማዋ መሃል ጠንካራ ግንብ ስለነበር ወንዶችና ሴቶች በሙሉ እንዲሁም የከተማዋ መሪዎች በሙሉ ወደዚያ ሸሹ። እነሱም ከውስጥ ሆነው በሩን ከዘጉት በኋላ የግንቡ አናት ላይ ወጡ። 52 አቢሜሌክም ወደ ግንቡ ሄደ፤ ጥቃትም ሰነዘረበት። ግንቡንም በእሳት ለማቃጠል ወደ መግቢያው ተጠጋ። 53 ከዚያም አንዲት ሴት በአቢሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ በመልቀቅ ጭንቅላቱን ፈረከሰችው።+
-