የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 12:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከዚያም ናታን ወደ ቤቱ ሄደ።

      ይሖዋም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ በመቅሰፍት መታው፤ ልጁም ታመመ።

  • 2 ሳሙኤል 12:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ሲያይ ልጁ እንደሞተ ገባው። በመሆኑም አገልጋዮቹን “ልጁ ሞተ?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ሞቷል” ብለው መለሱለት።

  • 2 ሳሙኤል 13:10-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በዚህ ጊዜ አምኖን ትዕማርን “በእጅሽ እንድታጎርሺኝ ምግቡን* ወደ መኝታ ክፍል አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም የጋገረችውን ቂጣ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወደነበረበት መኝታ ክፍል ገባች። 11 እሷም ምግቡን እንዲበላ ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና “እህቴ ሆይ፣ ነይ፣ አብረሽኝ ተኚ” አላት። 12 እሷ ግን እንዲህ አለችው፦ “ወንድሜ ሆይ፣ ይሄማ ፈጽሞ አይሆንም! እባክህ አታዋርደኝ፤ በእስራኤል ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ተደርጎ አያውቅም።+ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽም።+ 13 እኔስ ብሆን ይህን ነውሬን ተሸክሜ እንዴት እኖራለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ውስጥ ካሉት ወራዳ ሰዎች እንደ አንዱ ትቆጠራለህ። ስለዚህ አሁን፣ እባክህ ንጉሡን አነጋግረው፤ እሱም ቢሆን እኔን አይከለክልህም።” 14 እሱ ግን ሊሰማት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ኃይል ተጠቅሞ በማስነወር አዋረዳት። 15 ከዚያም አምኖን እጅግ በጣም ጠላት፤ ለእሷ ያደረበት ጥላቻም ለእሷ ከነበረው ፍቅር በለጠ። አምኖንም “ተነሽ ውጭልኝ!” አላት።

  • 2 ሳሙኤል 15:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ዳዊትም በኢየሩሳሌም አብረውት የነበሩትን አገልጋዮቹን በሙሉ ወዲያውኑ እንዲህ አላቸው፦ “ተነሱ፣ እንሽሽ፤+ አለዚያ አንዳችንም ከአቢሴሎም እጅ አናመልጥም! በፍጥነት መጥቶ እንዳይዘንና እንዳያጠፋን፣ ከተማዋንም በሰይፍ እንዳይመታ ቶሎ ብለን ከዚህ እንሂድ!”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ