2 ከዚያም ዳዊት የማልካምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ 3 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው።+ ዳዊት በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።