15 በኋላም ኩሲ ካህናት የሆኑትን ሳዶቅንና አብያታርን+ እንዲህ አላቸው፦ “አኪጦፌል እንዲህ እንዲህ በማለት አቢሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች መክሯቸው ነበር፤ እኔ ደግሞ እንዲህ እንዲህ ብዬ መክሬያቸዋለሁ። 16 አሁንም ለዳዊት ፈጥናችሁ መልእክት በመላክ እንዲህ ብላችሁ አስጠንቅቁት፦ ‘ዛሬ ሌሊት በምድረ በዳው ባሉት መልካዎች እንዳታድር፤ የግድ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ንጉሡና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ያልቃል።’”+