-
መዝሙር 18:31-42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+
ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?+
33 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+
34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤
ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ።
37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤
ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም።
38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቃቸዋለሁ፤+
እግሬ ሥር ይወድቃሉ።
39 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤
ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+
41 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤
ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም።
42 በነፋስ ፊት እንዳለ አቧራ ፈጽሜ አደቃቸዋለሁ፤
በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ አውጥቼ እጥላቸዋለሁ።
-