12 ከእሱ ቀጥሎ የአሆሐያዊው+ የዶዶ ልጅ አልዓዛር ነበር።+ እሱም ከሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች መካከል አንዱ ነው። 13 ፍልስጤማውያን ለጦርነት ተሰብስበው በነበረበት ጊዜ በጳስዳሚም+ ከዳዊት ጋር አብሮ ነበር። በዚያም የገብስ ሰብል የሞላበት መሬት ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጤማውያን የተነሳ ከአካባቢው ሸሹ። 14 እሱ ግን በእርሻው መካከል ካለበት ንቅንቅ ሳይል መሬቱ እንዳይያዝ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም መታቸው፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ድል አጎናጸፈ።+