-
2 ዜና መዋዕል 1:7-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በዚያ ሌሊት አምላክ ለሰለሞን ተገልጦ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ጠይቅ” አለው።+ 8 በዚህ ጊዜ ሰለሞን አምላክን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተኸዋል፤+ በእሱም ምትክ አንግሠኸኛል።+ 9 አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም፤+ እንደ ምድር አፈር እጅግ ብዙ በሆነ ሕዝብ+ ላይ አንግሠኸኛልና። 10 ይህን ሕዝብ መምራት* እንድችል ጥበብና እውቀት ስጠኝ፤+ አለዚያማ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?”+
-