-
ሕዝቅኤል 41:6, 7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች ከበላያቸው ሁለት ፎቅ ነበራቸው፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ 30 ክፍሎች ነበሩ። በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ፣ በጎን በኩል ያሉትን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም እነዚህ ተሸካሚዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም።+ 7 በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ጠመዝማዛ መተላለፊያ* ነበር፤ ላይ ወደሚገኙት ክፍሎች ሲወጣ የመወጣጫዎቹ ወርድ ይጨምር ነበር።+ አንድ ሰው ከታች ተነስቶ በመካከለኛው ፎቅ በኩል ወደ መጨረሻው ፎቅ ሲወጣ ፎቁ እየሰፋ ይሄድ ነበር።
-