ዘፍጥረት 3:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ። ዘፀአት 25:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሁለት የወርቅ ኪሩቦችን ትሠራለህ፤ ወርቁን በመጠፍጠፍም በመክደኛው ጫፍና ጫፍ ላይ ወጥ አድርገህ ትሠራቸዋለህ።+ 1 ነገሥት 6:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ከዚያም ኪሩቦቹን+ ውስጠኛው ክፍል* ውስጥ አስቀመጣቸው። የኪሩቦቹም ክንፎች ተዘርግተው ስለነበር የአንደኛው ኪሩብ ክንፍ አንደኛው ግድግዳ ጋ፣ የሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላኛው ግድግዳ ጋ ይደርስ ነበር፤ ወደ ቤቱ መሃል የተዘረጉት ክንፎቻቸው ደግሞ ይነካኩ ነበር። 2 ዜና መዋዕል 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እሱም ቤቱን፣ ወራጆቹን፣ ደፎቹን፣ ግድግዳዎቹንና በሮቹን በወርቅ ለበጣቸው፤+ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቦችን ምስል ቀረጸ።+ ሕዝቅኤል 41:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። 18 ግንቡ ኪሩቤልና+ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤+ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።
24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።
27 ከዚያም ኪሩቦቹን+ ውስጠኛው ክፍል* ውስጥ አስቀመጣቸው። የኪሩቦቹም ክንፎች ተዘርግተው ስለነበር የአንደኛው ኪሩብ ክንፍ አንደኛው ግድግዳ ጋ፣ የሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላኛው ግድግዳ ጋ ይደርስ ነበር፤ ወደ ቤቱ መሃል የተዘረጉት ክንፎቻቸው ደግሞ ይነካኩ ነበር።
17 ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። 18 ግንቡ ኪሩቤልና+ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤+ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።