-
2 ሳሙኤል 8:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 በመሆኑም ቶአይ የንጉሥ ዳዊትን ደህንነት እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከው (ምክንያቱም ሃዳድኤዜር ከቶአይ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበር)፤ እሱም ከብር፣ ከወርቅና ከመዳብ የተሠሩ ዕቃዎችን ይዞ መጣ። 11 ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃዎች ተገዢዎቹ ካደረጋቸው ብሔራት ሁሉ ላይ ወስዶ ከቀደሰው ብርና ወርቅ ጋር አብሮ ለይሖዋ ቀደሳቸው፤+ 12 ዕቃዎቹም ከሶርያ፣ ከሞዓብ፣+ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ላይ የወሰዳቸው እንዲሁም የሬሆብ ልጅ ከሆነው ከጾባህ ንጉሥ ከሃዳድኤዜር+ ላይ የማረካቸው ናቸው።
-