-
ዘፀአት 25:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ኪሩቦቹ ሁለቱን ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይከልሉታል፤+ እነሱም ትይዩ ይሆናሉ። የኪሩቦቹ ፊት ወደ መክደኛው ያጎነበሰ ይሆናል።
-
-
2 ዜና መዋዕል 5:8-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 የኪሩቦቹ ክንፎች ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ተዘርግተው ስለነበር ኪሩቦቹ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን+ ከላይ ሸፍነዋቸው ነበር። 9 መሎጊያዎቹ ረጅም ስለነበሩ የመሎጊያዎቹን ጫፎች ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ባለው በቅድስቱ ውስጥ ሆኖ ማየት ይቻል ነበር፤ ከውጭ ግን አይታዩም ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ። 10 የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ምድር ሲወጡ+ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን+ በገባበት ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች+ በስተቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።
-