ዘፀአት 40:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ቀጥሎም የምሥክሩን ጽላቶች+ ወስዶ በታቦቱ+ ውስጥ አስቀመጣቸው፤ የታቦቱንም መሎጊያዎች+ አስገባቸው፤ መክደኛውንም+ በታቦቱ ላይ አደረገው።+ ዘዳግም 10:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤+ ይሖዋም ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን፣ በሠራሁት ታቦት ውስጥ አስቀመጥኳቸው። እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ።