-
2 ዜና መዋዕል 7:19-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ሆኖም ጀርባችሁን ብትሰጡ፣ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ደንቦቼንና ትእዛዛቴን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ፣+ 20 እስራኤልን ከሰጠሁት ምድሬ ላይ እነቅለዋለሁ፤+ ለስሜ የቀደስኩትንም ይህን ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ፤ በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና* መሳለቂያ አደርገዋለሁ።+ 21 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል። በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ+ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ።+ 22 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን+ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ትተው+ ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው።+ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+
-