2 ዜና መዋዕል 9:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የሳባ ንግሥት+ ስለ ሰለሞን ዝና በሰማች ጊዜ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች* ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣ በጣም ብዙ ወርቅና+ የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ነበር። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው።+ 2 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ሰለሞን ሊያብራራላት ያልቻለው* ምንም ነገር አልነበረም። ማቴዎስ 12:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 የደቡብ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትኮንነዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+
9 የሳባ ንግሥት+ ስለ ሰለሞን ዝና በሰማች ጊዜ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች* ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣ በጣም ብዙ ወርቅና+ የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ነበር። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው።+ 2 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ሰለሞን ሊያብራራላት ያልቻለው* ምንም ነገር አልነበረም።
42 የደቡብ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትኮንነዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+