17 በተጨማሪም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።+ 18 ወደ ዙፋኑ የሚያስወጡ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ ከዙፋኑም ጋር የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር ማሳረፊያ ነበር፤ መቀመጫውም በጎንና በጎኑ የእጅ መደገፊያዎች ያሉት ሲሆን ከእጅ መደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች+ ቆመው ነበር። 19 በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር አንድ አንድ አንበሳ፣ በአጠቃላይ 12 አንበሶች+ ቆመው ነበር። እንዲህ ያለ ዙፋን የሠራ አንድም ሌላ መንግሥት አልነበረም።