የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 16:30, 31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ።

  • 2 ነገሥት 3:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እሱም ለ12 ዓመት ገዛ።

  • 2 ነገሥት 3:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ይሁንና የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ+ የተከተለውን የኃጢአት ጎዳና የሙጥኝ አለ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም።

  • 2 ነገሥት 10:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ኢዩ ግን በሙሉ ልቡ በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ሕግ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም።+ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+

  • 2 ነገሥት 13:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ+ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በ23ኛው ዓመት የኢዩ+ ልጅ ኢዮዓካዝ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። 2 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ እንዲሁም የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት መሥራቱን ቀጠለ።+ ከዚያም አልራቀም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ