ዘፀአት 20:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፤ በእሱም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣* መንጎችህንና ከብቶችህን ሠዋ። ስሜ እንዲታወስ በማደርግበት ቦታ ሁሉ+ ወደ አንተ እመጣለሁ፣ ደግሞም እባርክሃለሁ። ዘዳግም 12:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።+ 6 የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣+ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣+ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን+ እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት+ የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው። 1 ነገሥት 8:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም፤+ ዳዊትን ግን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን መረጥኩ።’ 17 አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር።+
24 ከጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፤ በእሱም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣* መንጎችህንና ከብቶችህን ሠዋ። ስሜ እንዲታወስ በማደርግበት ቦታ ሁሉ+ ወደ አንተ እመጣለሁ፣ ደግሞም እባርክሃለሁ።
5 ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።+ 6 የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣+ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣+ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን+ እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት+ የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው።
16 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም፤+ ዳዊትን ግን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን መረጥኩ።’ 17 አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር።+