9 በመሆኑም የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ። እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ።+ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።+ 10 በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ አለቆች ሰጣቸው። 11 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ገብተው ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር።