ዘዳግም 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+ 2 ነገሥት 18:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ+ ልጅ ሕዝቅያስ+ ነገሠ። 2 ነገሥት 18:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እሱ ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠራ ነበር። 2 ዜና መዋዕል 34:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ 2 ዜና መዋዕል 34:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በተጨማሪም እሱ በተገኘበት የባአልን መሠዊያዎች አፈራረሱ፤ በላያቸው ላይ የነበሩትንም የዕጣን ማጨሻዎች ሰባበራቸው። ደግሞም የማምለኪያ ግንዶቹን፣* የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* ሰባብሮ አደቀቃቸው፤ ከዚያም ለእነሱ ይሠዉ በነበሩት ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።+
5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+
4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እሱ ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠራ ነበር።
4 በተጨማሪም እሱ በተገኘበት የባአልን መሠዊያዎች አፈራረሱ፤ በላያቸው ላይ የነበሩትንም የዕጣን ማጨሻዎች ሰባበራቸው። ደግሞም የማምለኪያ ግንዶቹን፣* የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* ሰባብሮ አደቀቃቸው፤ ከዚያም ለእነሱ ይሠዉ በነበሩት ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።+