9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ሠራህ፤+ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።+ 10 በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!+