16 ከዚያም በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል የሃናኒ+ ልጅ ወደሆነው ወደ ኢዩ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2 “ከአቧራ ላይ አንስቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አደረግኩህ፤+ አንተ ግን የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተልክ፤ ሕዝቤ እስራኤልም ኃጢአት እንዲሠራ አደረግክ፤ እነሱም በኃጢአታቸው አስቆጡኝ።+ 3 ስለሆነም ባኦስንና ቤቱን ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ፤ ቤቱንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤት አደርገዋለሁ።