-
ዘዳግም 28:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+
-
-
ዘዳግም 28:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ከራስህ በላይ ያለው ሰማይ መዳብ፣ ከበታችህ ያለውም ምድር ብረት ይሆንብሃል።+
-
-
ኤርምያስ 14:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?
ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ?
አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም?+
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክ
አንተን ተስፋ እናደርጋለን።
-