ዳንኤል 10:8-10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ይህን ታላቅ ራእይ በተመለከትኩ ጊዜም በውስጤ ምንም ኃይል አልቀረም፤ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁመናዬ ተለወጠ፤ ኃይሌም በሙሉ ተሟጠጠ።+ 9 ከዚያም ሲናገር ድምፁን ሰማሁ፤ ሆኖም ሲናገር እየሰማሁት ሳለ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፍቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ።+ 10 በዚህ ጊዜ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤+ ከቀሰቀሰኝ በኋላ በእጄና በጉልበቴ ተደግፌ እንድነሳ አደረገኝ። የሐዋርያት ሥራ 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሁንና የይሖዋ* መልአክ ድንገት መጥቶ ቆመ፤+ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ። ጴጥሮስን ጎኑን መታ አድርጎ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰውና “ቶሎ ብለህ ተነሳ!” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ።+
8 እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ይህን ታላቅ ራእይ በተመለከትኩ ጊዜም በውስጤ ምንም ኃይል አልቀረም፤ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁመናዬ ተለወጠ፤ ኃይሌም በሙሉ ተሟጠጠ።+ 9 ከዚያም ሲናገር ድምፁን ሰማሁ፤ ሆኖም ሲናገር እየሰማሁት ሳለ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፍቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ።+ 10 በዚህ ጊዜ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤+ ከቀሰቀሰኝ በኋላ በእጄና በጉልበቴ ተደግፌ እንድነሳ አደረገኝ።
7 ይሁንና የይሖዋ* መልአክ ድንገት መጥቶ ቆመ፤+ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ። ጴጥሮስን ጎኑን መታ አድርጎ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰውና “ቶሎ ብለህ ተነሳ!” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ።+