26 በመሆኑም ኢዮዓብ ከዳዊት ዘንድ ወጥቶ መልእክተኞችን ወደ አበኔር ላከ፤ እነሱም ሲራ ከተባለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ጋ መለሱት፤ ዳዊት ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። 27 አበኔር ወደ ኬብሮን+ በተመለሰ ጊዜ ኢዮዓብ ከእሱ ጋር በግል ለመነጋገር ነጠል አድርጎ ወደ ቅጥሩ በር ይዞት ገባ። ሆኖም በዚያ ሳሉ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው፤+ ይህን ያደረገው የወንድሙን የአሳሄልን ደም ለመበቀል ነው።+