2 ነገሥት 10:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 በዚያ ዘመን ይሖዋ የእስራኤልን ግዛት መቆራረስ* ጀመረ። ሃዛኤል በሁሉም የእስራኤል ግዛት ጥቃት ይሰነዝር ነበር፤+ 2 ነገሥት 12:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል+ ጌትን+ ለመውጋት የወጣው በዚህ ጊዜ ነበር፤ እሱም በቁጥጥር ሥር አዋላት፤ ከዚያም በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወሰነ።*+ 2 ነገሥት 13:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ+ በእስራኤል ላይ ነደደ፤+ በዘመናቸውም ሁሉ በሶርያ ንጉሥ በሃዛኤል+ እጅና በሃዛኤል ልጅ በቤንሃዳድ+ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። አሞጽ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ዓመፅ* ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም በብረት ማሄጃ ጊልያድን ወቅተዋል።+