18 ከዚህ ሁሉ በኋላ ይሖዋ በማይድን የአንጀት በሽታ ቀሰፈው።+ 19 ድፍን ሁለት ዓመት ከታመመ በኋላም ሕመሙ ጠንቶበት አንጀቱ ወጣ፤ በበሽታውም እጅግ ሲሠቃይ ቆይቶ በመጨረሻ ሞተ፤ ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርጉት እንደነበረው ለእሱ ክብር እሳት አላነደዱም።+ 20 በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለስምንት ዓመት ገዛ። ሲሞት ማንም አላዘነለትም። በመሆኑም በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ሳይሆን+ በዳዊት ከተማ+ ቀበሩት።