-
2 ዜና መዋዕል 21:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ በተቀመጠ ጊዜ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም ከእስራኤል መኳንንት መካከል የተወሰኑትን በሰይፍ በመግደል ሥልጣኑን አጠናከረ።+
-
-
2 ዜና መዋዕል 22:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ+ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተሰብ* በሙሉ አጠፋች።+ 11 ይሁንና የንጉሡ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት ሊገደሉ ከነበሩት የንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮዓስን+ ሰርቃ በመውሰድ እሱንና ሞግዚቱን በውስጠኛው መኝታ ክፍል አስቀመጠቻቸው። የንጉሥ ኢዮራም+ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት (የካህኑ ዮዳሄ+ ሚስትና የአካዝያስ እህት ነበረች) ከጎቶልያ ደብቃ አቆየችው፤ በመሆኑም ጎቶልያ ሳትገድለው ቀረች።+ 12 እሱም ከእነሱ ጋር ለስድስት ዓመት በእውነተኛው አምላክ ቤት ተደብቆ ቆየ፤ በዚህ ጊዜ ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ትገዛ ነበር።
-