ዘኁልቁ 11:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሙሴም ወጥቶ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲሁም ከሕዝቡ ሽማግሌዎች መካከል 70 ሰዎችን ሰብስቦ በድንኳኑ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።+ 25 ከዚያም ይሖዋ በደመና ወርዶ+ አነጋገረው፤+ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ+ ወስዶ በ70ዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገ። እነሱም ወዲያው መንፈሱ እንዳረፈባቸው እንደ ነቢያት አደረጋቸው፤*+ ሆኖም ዳግመኛ እንደዚያ አልሆኑም። ዘኁልቁ 27:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።+ ዘኁልቁ 27:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲሰማውም+ ከሥልጣንህ* የተወሰነውን ስጠው።+ 2 ነገሥት 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ዮርዳኖስን እንደተሻገሩ ኤልያስ ኤልሳዕን “ከአንተ ከመወሰዴ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ጠይቀኝ” አለው። ኤልሳዕም “እባክህ፣ መንፈስህ+ በእጥፍ* ይሰጠኝ”+ አለው።
24 ሙሴም ወጥቶ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲሁም ከሕዝቡ ሽማግሌዎች መካከል 70 ሰዎችን ሰብስቦ በድንኳኑ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።+ 25 ከዚያም ይሖዋ በደመና ወርዶ+ አነጋገረው፤+ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ+ ወስዶ በ70ዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገ። እነሱም ወዲያው መንፈሱ እንዳረፈባቸው እንደ ነቢያት አደረጋቸው፤*+ ሆኖም ዳግመኛ እንደዚያ አልሆኑም።
9 ዮርዳኖስን እንደተሻገሩ ኤልያስ ኤልሳዕን “ከአንተ ከመወሰዴ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ጠይቀኝ” አለው። ኤልሳዕም “እባክህ፣ መንፈስህ+ በእጥፍ* ይሰጠኝ”+ አለው።