34 ከዚያም ሙሴ ከሞዓብ በረሃማ ሜዳ ተነስቶ ወደ ነቦ ተራራ+ ይኸውም በኢያሪኮ+ ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ጲስጋ አናት+ ወጣ። ይሖዋም ምድሪቱን በሙሉ አሳየው፤ ይኸውም ከጊልያድ እስከ ዳን፣+ 2 ንፍታሌምን በሙሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ምድር፣ በስተ ምዕራብ በኩል እስካለው ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር በሙሉ፣+ 3 ኔጌብን፣+ የዮርዳኖስን አውራጃ+ እንዲሁም የዘንባባ ዛፍ ከተማ በሆነችው በኢያሪኮ ካለው ሸለቋማ ሜዳ አንስቶ እስከ ዞአር+ ድረስ አሳየው።