ዘፀአት 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+ መሳፍንት 10:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እነሱም ከመካከላቸው ባዕዳን አማልክትን አስወግደው ይሖዋን አገለገሉ፤+ በመሆኑም በእስራኤል ላይ እየደረሰ የነበረውን መከራ ሊታገሥ አልቻለም።* + መዝሙር 106:43, 44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+ 44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+
7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+
43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+ 44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+