ዘሌዋውያን 26:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እኔ ራሴ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤+ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁም በመደነቅ ይመለከቷታል።+ 33 እናንተንም በብሔራት መካከል እበትናችኋለሁ፤+ ሰይፍም መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፤+ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፤+ ከተሞቻችሁም ይፈራርሳሉ። ዘዳግም 4:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይሖዋም በሕዝቦች መካከል ይበትናችኋል፤+ ይሖዋ በሚበትናችሁ ብሔራትም መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።+ ዘዳግም 28:64 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+ 1 ነገሥት 14:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል፤+ ከወንዙም* ማዶ ይበትናቸዋል፤+ ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል።
32 እኔ ራሴ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤+ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁም በመደነቅ ይመለከቷታል።+ 33 እናንተንም በብሔራት መካከል እበትናችኋለሁ፤+ ሰይፍም መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፤+ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፤+ ከተሞቻችሁም ይፈራርሳሉ።
64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+
15 ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል፤+ ከወንዙም* ማዶ ይበትናቸዋል፤+ ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል።