-
1 ነገሥት 22:51አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ገዛ።
-
-
2 ነገሥት 23:4, 5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን፣+ በሁለተኛ ማዕረግ ያሉትን ካህናትና በር ጠባቂዎቹን ለባአል፣ ለማምለኪያ ግንዱና* ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች በሙሉ ከይሖዋ ቤተ መቅደስ እንዲያወጡ አዘዛቸው።+ ከዚያም ከኢየሩሳሌም ውጭ በቄድሮን ተዳፋት ላይ አቃጠላቸው፤ አመዱንም ወደ ቤቴል+ ወሰደው። 5 የይሁዳ ነገሥታት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ በነበሩት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ላይ የሚጨስ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ የሾሟቸውን የባዕድ አምላክ ካህናት አባረረ፤ በተጨማሪም ለባአል፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ዞዲያክ ለተባለው ኅብረ ከዋክብትና ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ+ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ የነበሩትን በሙሉ አባረረ።
-