-
ኢያሱ 23:12, 13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ 13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+
-
-
ኢሳይያስ 42:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣
እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው?
በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም?
-