-
1 ነገሥት 15:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ምክንያቱም ዳዊት በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ እንዲሁም ከሂታዊው ከኦርዮ ጋር በተያያዘ ከፈጸመው ነገር በስተቀር በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እሱ ከሰጠው ከየትኛውም ትእዛዝ ፈቀቅ አላለም።+
-
-
2 ነገሥት 20:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።
-
-
2 ዜና መዋዕል 31:20, 21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ሕዝቅያስ በመላው ይሁዳ ይህን አደረገ፤ በአምላኩ በይሖዋም ፊት ጥሩና ትክክል የሆነውን አደረገ፤ ለእሱም ታማኝ ነበር። 21 ከእውነተኛው አምላክ ቤት+ አገልግሎት ጋርም ሆነ ከሕጉና ከትእዛዙ ጋር በተያያዘ አምላኩን ይፈልግ ዘንድ የጀመረውን ሥራ ሁሉ፣ በሙሉ ልቡ አከናወነ፤ ደግሞም ተሳካለት።
-