2 ዜና መዋዕል 28:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ፍልስጤማውያን+ ደግሞ በይሁዳ የሚገኙትን የሸፌላንና+ የኔጌብን ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽን፣+ አይሎንን፣+ ገዴሮትን፣ ሶኮንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ቲምናንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ጊምዞንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ተቀመጡ። 19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው። ኢሳይያስ 14:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ንጉሥ አካዝ በሞተበት+ ዓመት የሚከተለው ፍርድ ተላለፈ፦ 29 “ፍልስጤማውያን ሆይ፣ የመቺያችሁ በትር ስለተሰበረአንዳችሁም ብትሆኑ ደስ አይበላችሁ። ከእባቡ ሥር+ መርዘኛ እባብ ይወጣልና፤+ዘሩም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* ይሆናል።
18 ፍልስጤማውያን+ ደግሞ በይሁዳ የሚገኙትን የሸፌላንና+ የኔጌብን ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽን፣+ አይሎንን፣+ ገዴሮትን፣ ሶኮንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ቲምናንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ጊምዞንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ተቀመጡ። 19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው።
28 ንጉሥ አካዝ በሞተበት+ ዓመት የሚከተለው ፍርድ ተላለፈ፦ 29 “ፍልስጤማውያን ሆይ፣ የመቺያችሁ በትር ስለተሰበረአንዳችሁም ብትሆኑ ደስ አይበላችሁ። ከእባቡ ሥር+ መርዘኛ እባብ ይወጣልና፤+ዘሩም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* ይሆናል።