1 ነገሥት 18:46 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 ሆኖም የይሖዋ እጅ በኤልያስ ላይ መጣ፤ እሱም ልብሱን ጠቅልሎ መቀነቱ ውስጥ በመሸጎጥ* ከአክዓብ ፊት ፊት እየሮጠ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ ሄደ። ሕዝቅኤል 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በከለዳውያን+ ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የይሖዋ ቃል የካህኑ የቡዚ ልጅ ወደሆነው ወደ ሕዝቅኤል* መጣ። በዚያም የይሖዋ ኃይል* በእሱ ላይ ወረደ።+ የሐዋርያት ሥራ 11:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የይሖዋም* እጅ ከእነሱ ጋር ነበር፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም አማኝ በመሆን ጌታን መከተል ጀመሩ።+