-
ኢሳይያስ 37:8-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ራብሻቁም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ለቆ እንደሄደ ሲሰማ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ከሊብናም ጋር ሲዋጋ አገኘው።+ 9 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የኢትዮጵያው ንጉሥ ቲርሃቅ “ከአንተ ጋር ሊዋጋ ወጥቷል” የሚል ወሬ ሰምቶ ነበር። እሱም ይህን በሰማ ጊዜ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በድጋሚ መልእክተኞች ላከ፦+ 10 “የይሁዳን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘የምትታመንበት አምላክህ “ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” ብሎ አያታልህ።+ 11 እነሆ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉ ፈጽመው በማጥፋት ያደረጉትን ነገር ሰምተሃል።+ ታዲያ አንተ ብቻ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃል? 12 አባቶቼ ያጠፏቸውን ብሔራት አማልክታቸው ታድገዋቸዋል?+ ጎዛን፣ ካራን፣+ ረጼፍና በቴልአሳር የነበሩት የኤደን ሕዝቦች የት አሉ? 13 የሃማት ንጉሥ፣ የአርጳድ ንጉሥ፣ የሰፋርዊም+ ከተሞች ንጉሥ እንዲሁም የሄና እና የኢዋ ነገሥታት የት አሉ?’”
-