-
2 ነገሥት 12:11, 12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 የተቆጠረውን ገንዘብ በይሖዋ ቤት በሚከናወነው ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰዎች ይሰጧቸዋል። እነሱ ደግሞ ገንዘቡን በይሖዋ ቤት ለሚሠሩት አናጺዎችና የግንባታ ባለሙያዎች ይከፍሉ ነበር፤+ 12 በተጨማሪም ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ይከፍሉ ነበር። ደግሞም በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን ለመጠገን የሚውሉ ሳንቃዎችንና ጥርብ ድንጋዮችን ለመግዛት እንዲሁም ቤቱን ለመጠገን የሚያስፈልጉትን ሌሎች ወጪዎች ለመሸፈን ያውሉት ነበር።
-
-
2 ዜና መዋዕል 34:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከዚያም በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሠራተኞች ገንዘቡን ሰጧቸው። በይሖዋ ቤት የሚሠሩት ሠራተኞች ደግሞ ቤቱን ለመጠገንና ለማደስ አዋሉት።
-